Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address በስልጤ ዞን ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪ.ሜ ሲሆን 176 ኪ.ሜ አስፋልት እና 45 ካ.ሜ ፒስታ መንገድ ነው ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251912288101
  • Website
  • Deadline10 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-03-10 00:00:00
  • Categories Supply of Water

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለእመዣር ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት የውሃ ማከማቻ (Water Supply Reservoir) በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።


የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ /ቤት ለእመዣር ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት የውሃ ማከማቻ (Water Supply Reservoir) በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ፡- ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለግንባታው የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በምስ/አዘ/በር/ወረዳ ፋይናንስ /ቤት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በመምጣት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ።

በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች GC-6/የውሃ ስራዎች ተቋራጭ ደረጃ 6 / እና ከዛ በላይ

1.       ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸው የታደሰ የንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ከግብር ሰብሳቢ /ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ ማስረጃና ሌሎች ሰነዶችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

2.       ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ /ቤት ስም አሰርተው ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለባቸው ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

3.       ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።

4.       ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.       ጨረታው 15ኛው ቀን 800 ሰዓት ታሽጎ በቀኑ 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል። የግንባታው ሳይት (ቦታ) በምስ/አዘ//ወረዳ እመዣር ቀበሌ ውስጥ ነው።

6.       በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ ፋይናንሻል ዋጋዎች እና የግንባታ ስራው ቴክኒካል የማወዳደሪያ ሀሳብ ደጋፊ ሰነዶች በግልጽና በጥራት የሚታዩና ስርዝ ወይም ድልዝ ያልሆኑ መሆን አለባቸው።

7.       መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8.       የወረዳው ከተማ (ቂልጦ) ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪሎ ሜትር ሲሆን 176 ኪሎ ሜትር አስፓልት እና 45 ኪሎ ሜትር ፒስታ መንገድ ነው

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 27 17 59 14 / 09 33 62 02 20

 

በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ /ቤት

Save Tender