Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር
  • Address ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116733497
  • Website
  • Deadline28 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-02-28 00:00:00
  • Categories Hand Tools And Workshop Equipment , Equipment

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ. ማኅበር የወርክ ሾፕ ዕቃዎች፣ ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EAC 027/2018

 

1.       ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ. ማኅበር የወርክ ሾፕ ዕቃዎች፣ ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

2.       ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከየካቲት 17 ቀን 2018 . ጀምሮ እስከ የካቲት 24 ቀን 2018 . ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 230-630 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ 730-1100 ድረስኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ. ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎር አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

3.       ተጫራቾች የሚያቀርቡት

v  አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ

v  አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣

v  ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት።

v  በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል።

v  ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።

4.       ተጫራቾች የወርክሾፕ ዕቃዎች ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P. O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ. በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5.       የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ከየካቲት 21 ቀን 2018 . እስከ ጠዋቱ 430 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ከየካቲት 21 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ተፈጻሚ ይሆናል።

6.       ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን።

7.       ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 667 6204 ፋክስ ቁጥር 011 673 2006 መጠቀም ይችላሉ።

8.       ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ. ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ. ማኅበር

Save Tender