Tender Detail

Tender Details

  • Company ELFORA Agro Industries PLC (ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር)
  • Address ላምበረት በሚገኘው አዲሱ የኤልፎራ ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251116461076
  • Websitehttps://www.midrocinvestmentgroup.com/poultry-products/
  • Deadline06 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-03-06 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Agricultural , Supply Of Animals

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በስሩ ለሚገኙ ለኮምቦልቻ እና መልጌ ወንዶ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ለእርድ አገልግሎት የሚያስፈልጉ እና ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚቀርቡ ወንድ የዳልጋ ከብቶች ሆኖ ክፍያው ስጋው ተመልምሎ በሚገኘው መጠን ሆኖ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ከሚችሉ ልምድና ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር EL/LP-03/2026

 

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ /የተ/የግ/ማኅበር በስሩ ለሚገኙ ለኮምቦልቻ እና መልጌ ወንዶ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ለእርድ አገልግሎት የሚያስፈልጉ እና ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚቀርቡ ወንድ የዳልጋ ከብቶች ሆኖ ክፍያው ስጋው ተመልምሎ በሚገኘው መጠን ሆኖ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ከሚችሉ ልምድና ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የቁመና ክብደታቸውም ኮምቦልቻ ምግብ ማቀነባበሪያ የሚያስፈልጉ ከብቶች-

·        ብዛታቸው 9410 በሳምንት 408 በአጠቃላይ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት 9410 ከብቶችን ለማቅረብ የሚችሉ እና ሙሉ የስጋ ይዘት ያላቸው ያልከሱ በቆዳቸው ላይ ጉዳት (ጠባሳ) የሌላቸው ክፍያው ስጋው ተመልምሎ በሚገኘው ኪግ የሚሆን ሲሆን የርክክብ ሂደቱ ባለሙያዎች በሚያወጡት መስፈርት መሆን አለባቸው፡፡

·        ተረፈ ምርት ሙሉ በሙሉ የገዥ ይሆናል፡፡

እንዲሁም ለመልጌ ወንዶ ምግብ ማቀነባበሪያ የሚያስፈልጉ ከብቶች፡-

·        ብዛታቸው 3925 በሳምንት 162 በአጠቃላይ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት 3925 ከብቶችን ለማቅረብ የሚችሉ እና ሙሉ የስጋ ይዘት ያላቸው፣ ያልከሱ በቆዳቸው ላይ ጉዳት (ጠባሳ) የሌላቸው ክፍያው ስጋው ተመልምሎ በሚገኝው . የሚሆን ሲሆን የርክክብ ሂደቱ ባለሙያዎች በሚያወጡት መስፈርት መሆን አለባቸው፡፡

·        ተረፈ ምርት ሙሉ በሙሉ የገዥ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

አቅርቦቱ ወንድ የዳልጋ ከብቶች ሲሆኑ እንዲሁም ሴት የዳልጋ ከብቶች የሚቀርቡ ከሆነ በግብርና ሚኒስቴር መመሪያ ቁጥር 13/54/1/11 12/02/2014 . መሠረት ብቻ ይሆናል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

·        ተጫራቾች አግባብነት ያለው ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

·        ተጫራቾች የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከማኅበራት ውጪ ያሉት ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው

·        ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚመለስ ብር ለእያንዳንዱ ምድብ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

·        ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ለመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ጠቅላላ ካሸነፈው አቅርቦት ክፍያ ተመመጣኝ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።

·        ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ በተዘረዘረው እና በተያያዘው የአቅርቦትና የጥራት መሥፈርት መሠረት ጨረታው መጫረት ይችላሉ፡፡

·        ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 200 ሰዓት እስከ ቀኑ 11 ሰዓት እንዲሁም ከጠዋቱ 200 ሰዓት ቅዳሜ እስከ ቀኑ 600 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ላም በረት አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ አቅርቦት መምሪያ ክፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ

·        ተጫራቾች ሰነዳቸውን እስከ የካቲት 27 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት ላምበረት በሚገኘው አዲሱ የኤልፎራ ሕንጻ ሦስተኛ ፎቅ ይከፈትና ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይካሄዳል፡፡

·        ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 116461076 /0911867645/+251 911625992 /0927718699 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ /የተ/የግ/ማኅበር

Save Tender