የሀዋሳ ከተማ ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል በግልጽ ጨረታ ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ህጋው ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ መካከል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል በግልጽ ጨረታ ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ህጋው ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ መካከል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. SPLIT A CONDIONER ግዥ ሎት 01/2018
2. የወንበር እና የድንኳን ኪራይ ሎት 92/2018
3. በተለያዩ መድረኮች የማስተዋወቅና ሳውንድ ሲስተም ኪራይ ሎት 03/2018
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡-
1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ ፣
5. የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ በአዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ/ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለio (ለአስር) ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ - ሎት/ 01/ 100,000 ብር (አንድ መቶ ሺህ ብር)፣ ሎት 02 እና ሎት 3 ላይ 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የተመሰከረ ሲፒኦ CPO ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ኮፒ ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ለሎት 01 በማያያዝ እና ለሎት 02 እና 03 ላይ ፋይናንሻል ብቻ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 አሥር) ተከታይ ቀናት…… መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዥ ኬዝ ቲም) ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ።
ስልክ ቁጥር 0466 212 1334
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና መምሪያ
