የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት ለቶምቦላ ሎተሪ ዕጣ ሽልማት አገልግሎት የሚውል በኤሌክትሪክና በነዳጅ የሚሠራ ባለ ሰባት መቀመጫ ሃይብሪድ መኪና በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር ከአስመጪ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ኢሎአ/08/2018
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት ለቶምቦላ ሎተሪ ዕጣ ሽልማት አገልግሎት የሚውል በኤሌክትሪክና በነዳጅ የሚሠራ ባለ ሰባት መቀመጫ ሃይብሪድ መኪና በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር ከአስመጪ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000004652782 ገቢ በማድረግ ዋናውን ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
ተጫራቾች በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ በማስያዝ ዋናውን ማስረጃ ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶችን የቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂ ለየብቻው በፖስታ በማድረግና በፅሁፍ በመለየት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ክሊራንስ፣ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገባበት ቅፅ ሞልታችሁ ማህተምና ፊርማ አድርጋችሁ የመጫረቻ ሰነዶቻችሁን አሟልታችሁ በማቅረብና የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታወን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-78-16 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
