የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች በምድብ የተገለጹ ዝርዝሮች በዘርፉ ከተሰማሩ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ግ005/2018 በጀት ዓመት
የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች በምድብ የተገለጹ ዝርዝሮች በዘርፉ ከተሰማሩ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
|
ምድብ ቁጥር |
አገልግሎት/የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ ሰነድ ዋጋ |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ምድብ 1 |
ገረጋንቲ ድንጋይ |
400.00 |
150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) በሲፒኦ |
|
ምድብ 2 |
ቦልድ ድንጋይ |
400.00 |
130,000.00 (አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ) በሲፒኦ |
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች:-
1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ የንግድ ምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ መዝገባ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ድረ-ገጽ www.PPA.gov.et) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፤ በተጨማሪም በህግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ ለሰብ ቤዝ (የተቆፋሪ ማዕድን) ለማውጣትና ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል የማምረቻ ቦታ ኳሪ እና የባለቤትነት ፍቃድ፤ ወይም በሰነዶች መረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ውክልና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በተገለጸው ዋጋ የማይመለስ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ 9ኛ ፎቅ መግዛት ይችላሉ።
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ከሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ መሆን ይኖርባቸዋል።
4. አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋው 10% (አስር በመቶ) በግዥ አፈፃጸም መመሪያ መሠረት ማስያዝ የሚችል
5. ተጫራቾች ለጨረታው የሚያቀርቡት ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ለየብቻው ለይተው በፖስታ አሽገው ስም እና አድራሻ በግልፅ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባችዋል።
6. ጨረታው የሚከፈተበት ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለብት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ11ኛ የስራ ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቴክኒካል ሰነዱ በመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት 10ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታ ሚከፈትበት ቀን ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ሌላ ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኤጀንሲው አድራሻ፡- ፒያሳ በተለምዶ እሪ በከንቱ ተብሎ የሚጠራው ቀበሌ 15 ኢትዮ ሴራሚክስ
ጎን ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ፊት ለፊት ቢቲ ታዎር (ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር) ነው።
ስልክ ቁጥር ፡- 251-011-275-0002
በአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ
