Tender Detail

Tender Details

  • Company National Election Board of Ethiopia (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ)
  • Address ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 115153468
  • Websitehttps://nebe.org.et/
  • Deadline08 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2026-04-08 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo , Equipment

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ለማስፈፀም ለድምጽ አሰጣጥ ስልጠና እና የኦፕሬሽን ቁሳቁስ ስርጭት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር NEBE/NCB/12/2018

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ለማስፈፀም ለድምጽ አሰጣጥ ስልጠና እና የኦፕሬሽን ቁሳቁስ ስርጭት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ምድብ አንድ፣ ለድምጽ አሰጣጥ የስልጠና ቁሳቁስ ስርጭት የጭነት ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ

ምድብ ሁለት፡- ለድምጽ አሰጣጥ ኦፕሬሽን ቁሳቁስ ስርጭት የጭነት ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ

1.       በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 ማግኘት ይችላሉ።

2.       በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሠርተፍኬት የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሠርተፍኬት እና በመንግስት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3.       ተወዳዳሪዎች በሚወዳደሩበት መስክ ያላቸውን መልካም አፈጻጸም የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4.       የጨረታ ሰነዱን ከቦርዱ የግዥ አስተዳደር የሥራ ክፍል በመውሰድ ሞልተው አግባብ ባለው አካል በመፈረም ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.       ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ፣

ለምድብ አንድ ብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ 00/100)

ለምድብ ሁለት ብር 150,000.00 (ብር አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ 00/100)

በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል።

6.       ተወዳዳሪዎች ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

7.       ጨረታው መጋቢት 30 ቀን 2018 . ከቀኑ 800 ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 830 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤

8.       ቦርዱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

አድራሻችን፡- ቦሌ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር፡-+251 11 515 3468

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

Save Tender