በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ አንድ የሰራተኞች ሰርቪስ /Midi bus/ መኪና እና አንድ ፒካፕ መኪና በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ለማቅረብ ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
ኬኢኮስመኬፋ 006/2018
በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ አንድ የሰራተኞች ሰርቪስ /Midi bus/ መኪና እና አንድ ፒካፕ መኪና በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ለማቅረብ ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ/2018 ዓ.ም/ ግብር የከፈሉ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ፡ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ጨረታውን መሣተፍ ይችላሉ፣
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ መኪና በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ ሀስካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ቅርንጫፍ ሽያጭ መስሪያ ቤት እና ከአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ከግዥ ክፍል ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ አስከ አርብ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ስፒኦ ማቅረብ አለባቸው፤
4. ተጫራቾች የእያንዳንዱን መኪና ቴክኒካል ኦፈርና ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 3 የተገለጹትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ፣ ከዚህ በተጨማሪ ፋይናንሻል አፈር ለብቻ በአንድ ፖስታ ታሽገው አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ የሽያጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን እስከ ሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሰነዶቹን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታዉ ዓርብ ሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ቴክኒካል አፈሩ ብቻ በዕለቱ ዓርብ ሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ የሽያጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ይከፈታል፡፡
6. የቴክኒካል ምዘና ያለፉት ብቻ ፋይናንሻል አፈራቸው አዲስ አበባ የሽያጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግድም፡፡
7. አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ 011 554 57 71
0920935336
በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ
