የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎቹን ከቀን 29/07/2018 ጀምሮ በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገለፃል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች -
1. የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
2. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተሸከርካሪ ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.RO) ማቅረብ የሚችል፤
3. በግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
4. ተጫራቹ በጨረታ አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካሪ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤
5. ተሽከርካሪ አሽንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
6. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
7. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
8. ማንኛውም ተጫራች ተሸከርካሪውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
9. ተጫራቹ ተሸከርካሪውን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም
10. ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ ከቀን 29/07/2018 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉምክ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በቀን 03/08/2018 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
N.B
· አሸናፊው ተጨማሪ ስሌት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቀ፤ መኪናውን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።
· የሻንሲ እና የሞተር ቁጥር የተመታ ተሽከርካሪ ገዝተው መንገድ ትራንስፖርት ሰሌዳ ቁጥር ሲያወጡ መሸጥ እና መለወጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው ሰሌዳ በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት ሰሌዳ ቁጥር ሲያወጡ መሸጥ እና መለወጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት በኩል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
