ድርጅታችን ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር ለጋራዥ አገልግሎት የሚውል ደረጃውን የጠበቀ ሁለት ዓይነት የመኪና ማንሻ ሊፍቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ለመኪና ማንሻ ሊፍቶች ግዥ የወጣ የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር004/2018
ድርጅታችን ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር ለጋራዥ አገልግሎት የሚውል ደረጃውን የጠበቀ ሁለት ዓይነት የመኪና ማንሻ ሊፍቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. የመኪና ማንሻ ሊፍት Two Post Car Lift 10, 000 lbc (4.536kg) or 4.5 Ton ብዛት አስራ አምስት (15).
2. የመኪና ማንሻ ሊፍት Two Post Car Lift 12,000 lbs (5.443 kg) or 5.5 Ton ብዛት አምስት (05)
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. የታደሰ የዘርፉ ንግድ ፈቃድ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር)
3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ቫት ምዝገባ ሠርተፍኬት)
5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ 2% የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
6. ጨረታው በሁለት ኤንቨሎፕ የሚካሄድ በመሆኑ ተጫራቾቾ የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶችን ለብቻ በመለየት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ አዲስ አበባ አደይ አበባ አካባቢ በሚገኘው ኢካፍኮ አ/ማህበር መ/ቤት ሽያጭ ክፍል 500 (ብር አምስት መቶ) መግዛት የሚትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነድ ሳጥን በ11ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን አውቀው የጨረታ ሰነድ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ። ሌሎች መስፈርቶች ከጨረታው ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0114421775
ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር
