የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ ሰነዱ ላይ በቀረበው መስፈረት መሰረት መኪናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ ሰነዱ ላይ በቀረበው መስፈረት መሰረት መኪናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታ ሰነዱን ከኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ይህ ጨረታ በማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ተከታታይ ቀናት ብቻ መውሰድ ይቻላል፡፡
2. ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤ ቲን፣ ቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የ90 ቀን ዋስትና ያለው ቢድ ቦንድ፣ ሲፒኦ ከጨረታ መከፈቻ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በታሸገ ፖስታ (ኤንቨሎፕ) የድርጅቱን ማህተም በመምታት ከዶከመንት ጋር ለብቻው ተያይዞ መቅረብ አለበት።
4. ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት
· ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ (ኤንቨሎፕ) የድርጅቱን ማህተም በመምታት በ22ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
· ጨረታው በዚሁ ዕለት 4፡00 ሰዓት የሚዘጋ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
· የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
5. የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ሙሉ ለሙሉ ላሟሉ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ታይቶ አሸናፊው ተጫራች ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል።
· ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች በሙሉ አሟልተው የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሠረዙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
· ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OACF ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12
ስልክ ቁጥር፡- 0910545442
የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ
