የዓዲግራት ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ለሴፍቲኔት ፕሮግራም ግልጋሎት የሚውል የኢንዳስትርያል ማቴሪያል /industrial material /፣ ሎካል ማቴሪያል /Local material/፣ ብሎኬት በአለም ባንክ ለፕሮጀክት ማስፈፀምያ ተብሎ ከፀደቀ በጀት በሃገራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የዓዲግራት ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ለሴፍቲኔት ፕሮግራም ግልጋሎት የሚውል
በሎት-1 የኢንዳስትርያል ማቴሪያል /industrial material /፣
በሎት 2 ሎካል ማቴሪያል /Local
በሎት-3 ብሎኬት በኣለም ባንክ ለፕሮጀክት ማስፈፀምያ ተብሎ ከፀደቀ በጀት በሃገራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ስለሚፈልግ
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ለምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
* ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ መለያ ቁጥር /Tin No/፣ የዘመኑ የታደሰ የመቅረባይነት ሰርተፊኬት/በኦን ላየን በፌዴራል በአቅረባይነት ዝርዝር የተመዘገበበት ማስረጃ፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬትና ጊዜው ያላላፈው የቫት ዲክላሬሽን ቅጂ ከዋናው ዶክመንት ማቅረብ የሚችል።
* ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ይህ ምልክታ ጨረታ ከወጣበት ቀን 1 ሚያዝያ 2018 ዓ.ም እስከ ቀን 30 ሚያዝያ 2018 ዓ/ም 11:30 ሰዓት የማይመለስ ብር 400.00 /ኣራት መቶ እየከፈላችሁ ከዓዲግራት ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት በግዥ ቢሮ ቁጥር 7 ሰነድ መውሰድ ትችላላችሁ።
* ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ ሰዓት በፊት ለሎት- 1 ለኢንዳስትርያል ማቴሪያል/industrial material/ በኢትዮዽያ ገንዘብ 50000.00 /ኣምሳ ሺ ብር/፣ ለሎት 2 ለሎካል ማተርያል/ Local material/ በኢትዮዽያ ገንዘብ 40000.00 /ኣርባ ሺ ብር/፣ ለሎት3 ለብሎኬት 20000 /ሃያ ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ክረዲት ሌተር፣ በሲፒኦ ወይ በጥሬ ገንዘብ የጨረታ ማስከበርያ ማስያዝ ኣለባቸው።
* የጨረታ ሳጥን በከተማ ዓዲግራት ዕቅድና ፋይናንስ የሚገኝ ሲሆን ይህ ምልክታ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተጫራቾች ክፍት ይሆናል።
* ጨረታው ግንበት 3/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በዓዲግራት ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ተጫራቾች ወይ ደሞ ወኪላቸው በተገኙበት ይከፈታል።
* የሚሞላው ዋጋ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ስርዝ ድልዝ ካጋጠመ የባለቤቱ ፊርማ መደረግ አለበት
* የጨረታ ኣሸናፊ የሚሆነው በየሎቱ በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ የሞላ ተጫራች ይሆናል
* የሚሞላው ዋጋ ከነቫቱ መሆኑና ኣለመሆኑ ሊገለፅ ይገባል፤ካልተገለፀ ደሞ የተሞላው ዋጋ ግዥ ፈፃሚ ኣካል ከነቫቱ መሆኑን ታሳቢ ያደርጋል።
* በእያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነድ ማህተምና ፊርማ የባለቤቱ መደረግ ይገባቸዋል።
* መስሪያ ቤታችን ይህ ጨረታ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስራ ሰዓት በኣካል ወደ ቢሯችን በመምጣት ወይም ደሞ በሞባይል ቁጥር፡- 0914123546 ወይም 0941336816 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ዓዲግራት ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት
