Tender Detail

Tender Details

  • Company የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ሐረር
  • Address , Phone: 0933342596
  • Website
  • Deadline04 May 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-05-04 00:00:00
  • Categories Equipment

የመ/ሰ/ማ/ዋ/አስ/ም/ሪጅን ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የመ/ሰ/ማ/ዋ/አስ/ም/ሪጅን ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ ንብረቶች አይነት ብዛት መነሻ ዋጋ ሴሎች መረጃዎች ከመደበኛ የጨረታ ሰነድ ጋር በሰንጠረዥ ያቀረበ ሲሆን

1.     አስተዳደሩ ለሽያጭ ያቀረባቸውን ያገለገሉ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር እቃዎችን ያገለገሉ ተሽከርካሪ ወንበር፣ የእንጨት ወንበር፣ የእንጨት ጠረፔዛ፣ ልዩ ልዩ የብረት በሮች እና መስኮቶች፣ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር፣ ፋይል ካቢኔት እና ልዩ ልዩ የመኪና እቃዎችን ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ለዚሁ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 200.00/ ሁለት መቶ ብር / በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

2.     ተጫራቾች የጨረታ ማቅረቢያውን ሞልተው ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነዱን ማስገባታቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።

3.     ለጨረታ የቀረቡት ያገለገሉ ንብረቶች የመነሻ ዋጋ በሰንጠረዡ በተዘረዘረው መሰረት ሲሆን ተጫራቹ ሊገዛ የሚፈለገውን ንብረቶች በመለየት የሚገዛበትን ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀው ማቅረቢያ ሰነድ በ 2 ቅጽ ሞልቶ ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ አለበት።

4.     ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ብር 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጨረታ መክፈቻው ቀን ቀደም ብሎ ማስያዝ ይኖርበታል።

5.     የጨረታ ማቅረቢያ ሰነዱ በታሸገ ፖስታ በፖስታው ላይ የተጫራቹ ሙሉ ስም አደራሻ እና ፊርማ መግለጽ አለበት።

6.     ለጨረታ ከላይ በተራ ቁጥር 4 በተመለከተው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ያላስያዘ ከጨረታው ይሰረዛል።

7.     ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ10 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ /ታሽጎ / 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ሆኖም ግን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በአካል ባይገኙም ጨረታው በሰዓቱ ይከፈታል።

8.     አስተዳደሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9.     ተጨማሪ መረጃ ከተፈለገ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡- ሐረር ከተማ ቀበሌ 14 ልዩ ስሙ ቦቴ

ስልክ ፡- 09 33 34 25 96 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።

 

የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ሐረር

Save Tender