በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ ለአሰላ 230/132/33/15 ኪ.ቮ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የግንባታ እቃዎች እና የተለያዩ ጣውላዎች ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/C/FP/
NCB/14/2018
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ ለአሰላ 230/132/33/15 ኪ.ቮ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የግንባታ እቃዎች እና የተለያዩ ጣውላዎች ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
· ተጫራቾች በኮንስትራከሽን ዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
· ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የካ ክ/ከ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት፣ የኢንጂነሪንግና ኮንስትራከሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
· ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ዕቃዎች በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝርበታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/EC/FP/NCB/14/2018 የሚል ምልክት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
የአቅርቦት ግዥ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ሎት 1 የግንባታ እቃዎች |
ብር 500,000.00 |
ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት |
|
ሎት 2 የተለያዩ ጣውላዎች |
ብር 100,000.00 |
⁕ ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
⁕ ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- +251 116 73 21 98 መደወል ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ
