የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (inflight catering) እና ለስካይላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የሀበሻ ዶሮ ከሚያቀርቡ ድርጅቶች ጋር በኮንትራት ስምምነት ለሦስት (3) ዓመት ለመሥራት ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመምረጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T613
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (inflight catering) እና ለስካይላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የሀበሻ ዶሮ ከሚያቀርቡ ድርጅቶች ጋር በኮንትራት ስምምነት ለሦስት (3) ዓመት ለመሥራት ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመምረጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
በአገልግሎቱ ዘርፍ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ፤ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ምዝገባ ወረቀት ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ፣ አንድ (1) ዓመትና እና ከዛ በላይ የሠራ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E- 99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T613 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሃምሳ ሺህ ብር (50,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፤
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር፡ 011-517-45-52
ብርቱኳን ሰሙ
ኢ-ሜይል: birtukans@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
