ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን የድርጅቱን በዋናው መ/ቤት ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ የመስክ መኪኖቹን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመኪኖች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን የድርጅቱን በዋናው መ/ቤት ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ የመስክ መኪኖቹን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መኪኖቹ በሚገኙበት አድራሻ ጉርድ ሾላ ቴን ሲስተር ህንፃ ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች የሚገዙትን መኪና ወይም ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የመኪናውን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /column/ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአኀዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ አዲስ አበባ ከተማ ጉርድ ሾላ ኤኤች ኤፍ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304 በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት አስተዳደርና ፋይናንስ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ ወይም በተወካዩ መፈረም አለበት፡፡
5. ተጫራቾች ጨረታው በተለያዩ የማስታወቂያ ሰሌዳዎችና በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ አለባቸው።
6. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ03 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ5 ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው። ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
7. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለአንድ መኪና የማይመለስ 500 ብር (አምስት መቶ ብር) እየከፈሉ ባሎት 07 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ሰባተኛው ቀን 6፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ መኪና መጫረት ከፈለጉ ተጨማሪ ሰነድ መግዛት አለባቸው፡፡
8. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በተለያዩ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 (ሰባት) የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በሰባተኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 10:00 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፊት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
9. ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነድ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
10. ድርጅቱ ላሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-647 83 82/0920 52 37 34 ወይም በአካል በመምጣት መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ጉርድ ሾላ ኤ.ኤች. ኤፍ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 304
ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዲቨሎፕመንት ኦርጋናዜሽን
