አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ/022/2018 Polyurethane based Sealant & Sealant Primer አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ/022/2018 Polyurethane based Sealant & Sealant Primer አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-
1. በዘርፉ የተሠማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)፣
2. በመንግሥት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣
3. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT Certificate)
5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)፣
6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (C.P.O) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደርይችላሉ፡፡
በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመከፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ሕንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ወይም 7-01 መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡ 0118 21 22 14
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
