Tender Detail

Tender Details

  • Company ETHIOPIAN RAILWAYS CORPORATION
  • Address , Phone: +251 117620049
  • Website
  • Deadline01 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-07-01 10:30:00
  • Categories Machinery Spare Parts

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በግዥ መለያ ቁጥር፦ 004/2018 ለባቡር እና ለባቡር መሰረተ-ልማት ጥገና የሚዉሉ የመለዋወጫ፤መሣሪያዎች፤አላቂ እቃዎች፤ዘይት እና ግሪስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡


ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በግዥ መለያ ቁጥር፦ 004/2018 ለባቡር እና ለባቡር መሰረተ-ልማት ጥገና የሚዉሉ የመለዋወጫ፤መሣሪያዎች፤አላቂ እቃዎች፤ዘይት እና ግሪስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ተ/ቁ የግዥ ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ
ሎት 1 ለጥገና አገልግሎት የሚዉሉ መሣሪያዎች ግዥ 150,000 (አንድ መቶ አምሳ ሺህ ብር)
ሎት 2 ለጥገና አገልግሎት የሚዉሉ መለዋወጫዎች ግዥ 150,000 (አንድ መቶ አምሳ ሺህ ብር)
ሎት 3 ለጥገና አገልግሎት የሚዉሉ አላቂ እቃዎች ግዥ 70,000 (ሰባ ሺህ ብር)
ሎት 4 ለጥገና አገልግሎት የሚዉሉ ዘይት እና ግሪስ ግዥ 70,000 (ሰባ ሺህ ብር)

 

1.በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣

3 የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣

  • የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው እና የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/ Tin No /ያላቸው
  • ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም የተዘጋጀ CPO እና የተረጋገጠ የባንክ ጋራንቲ ማሰራት ይኖርባቸዋል ፡፡ ነገር ግን CPO በተቀመጠዉ ሎት መሰረትያላስያዘ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፣
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የሚችሉት በሪፖርተር ጋዜጣ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡
  1. ማንኛውም ተጫራች ከተራ ቁጥር1 እስከ 6 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300(ሦስት መቶ) በድርጅቱ ስም በተከፈት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000493811049 በመክፍል ያስገቡበትን ዲፖዚት ስሊፕ ይዘዉ በመምጣት ዘውትር በስራ ሰዓት ቃሊቲ ማሰልጠኛ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት መግዛት ይችላሉ ፡፡
  2. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን የጠበቀ ዕቃ ካላቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፣
  1. መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፣ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በፖስታ አሽገው የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
  2. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው፣
  3. ጥቃቅንና አንስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸዉ ዕቃዎች የጨረታ ሰነዱን በነጻ ለመዉሰድ

ሀ.ከደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለበት

ለ.ሰነዱን በነጻ ለመዉሰድ በመመሪያ መሰረት ለምትወደደሩበት ዕቃ አምራች መሆን አለባቸሁ

  1. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ ወይም አገልግሎት ዝርዝር ላይ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም አሸናፋው የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መዋዋል አለበት ይህ ባይሆን ግን ለዋስትና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግሰት ገቢ ይሆናል፡፡
  2. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሚገኝው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሰኔ 24/2018 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  1. ጨረታው የሚከፈተው ሰኔ 24/2018 ዓም ጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይሆናል፡፡
  1.  መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት

ስልክ ቁጥር 0114708116

ሰኔ 10/2018

 

Save Tender