ጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ ጥበቃ እና ሴት ፈታሽ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አግልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው የሚወዳደሩ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር/004/26
ጎሕ ቤቶች ባንክ አ.ማ ጥበቃ እና ሴት ፈታሽ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አግልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው የሚወዳደሩ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ከፌደራል ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቅጥር/employment/ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶቹ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ ቅጅ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቲን የምስክር ወረቀት እና ከገቢዎች ሚኒስቴር ከግብር ነፃ መሆናቸውንና ጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከ 15/10/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ ሶስት መቶ ብር /300.00/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ /Bid Bond/ ብር 50‚000.00 ቢያንስ ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራች በስራው/በዘርፉ ለ3 ዓመታትና ከዚያ በላይ የቆየ መሆን አለበት ፤ ከሶስት ዓመት በታች ልምድ ያለው ድርጅት ተቀባይነት አይኖረውም
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፤
- በስልክ ቁጥር 0116686833/0116687376 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ወይም በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ቦሌ ጃፓን ኢምባሲ አርማህ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ የባንኩ የሰው ሃብትና ሰፕላይ ቼይን መምሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
