ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዬን ማህበር ለምርት ስራ አገልግሎት የሚውል Maize flour (Fine) በሀገር ውስጥ ግለጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማኅበር
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር WVD34/2018-09
1. ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዬን ማህበር ለምርት ስራ አገልግሎት የሚውል Maize flour (Fine) በሀገር ውስጥ ግለጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
2. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከአክሲዮን መህበሩ ቅ/ጽቤት አዲስ አበባ ወይንም ከዋናው መስሪያ ቤት ኮምቦልቻ መግዛት ይቻላል:: ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በትክክል በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ መስታወቂያው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራቀናት ውስጥ በጨረታ መመሪያውላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ,በ(C.P.O)ወይንም በባንክጋራንቲ በማስያዝ ኮምቦልቻ ዋናው መ/ቤት ወይም አድስ አበባ ቅ/ጽቤት ፓፓሲኖስ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 143 ወይም 144 እስከቀኑ 9 ሰዓት ማቅረብይችላሉ ::
3. ጨረታው ማስታወቂያው በተዘጋ በ3ኛው ቀን ኮምቦልቻ (ወሎ) በዋናው መስሪያ ቤት ከጧቱ 4 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
4. ይህ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል ::
5. አ/ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን መሉበሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
ስልክ ቁጥር - 033-5510627/5510211/0973424242
(ኮምቦልቻ)
