በጉምሩከ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኙ ተሸከርካሪዎች እና ባለሶስት እግርተሽከርካሪዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ጨረታ ቁጥር 005/2018
በጉምሩከ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኙ ተሸከርካሪዎች እና ባለሶስት እግርተሽከርካሪዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
በዚሁ መስረት ፡-
በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 005/2018 በ24/10/2018 ዓ.ም ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች ::
1. ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የታደሰ መታወቂያ ወይም የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ ያለው ያላት
2. ለጨረታ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ሲሆን የሚገኘው ድሬዳዋ ሙዲአነኖ ግቢ በሚገኘው ተሽከርካሪ መጋዘን ውስጥ ነው::
3. የተሽከረካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የሆነ ሰው በጨረታ መሳተፍ አይችልም::
4. በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለጸው መስፈርት መሰረት በመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና እያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ከ17/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ 6:00 ሰዓት ከሰዓት 8፡30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰአት እስከ 6፡00 ሰአት ድረስ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሰነዱን በመግዛት ተሸከርካሪው በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል፡፡
5. ተሽከርካረውን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
6. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ድሬዳዋ ሙዲአነኖ የሚገኘው ግቢ ውስጥ ነው::
7. ተጫራቾች ለተሽከርካሪው የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት ::
8. ተጫራቾች ተሽከርካሪውን በመግዛት በጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ በንግድ ባንክ የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል::
9. የሐራጅ ጨረታ የሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በዕለቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ጨረታው ይጀምራል፡፡
10. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒአ በሶስት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግባቸዋል፡፡
11. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ተሽከርካሪ አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ተሸከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል::
12. ከላይ በተራ ቁጥር 11 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ተሽከርካሪውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለሥልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ይቀርባል::
13. የጉምሩክ ኮሚሽን ድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤት ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0915460970 (0912885746) መደወል ይቻላል::
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
