የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት ያገስገሱ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ።
ያገስገሱ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር PPSP/VP-11FB/11/10 2018
የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ የግብርና ሚኒስቴር የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስርሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ፣ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣ የፌዴራል የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ መወዳደርይችላል፡፡
1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
2. ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ በመምጣት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ ገቢ በማድረግና ያስገቡበትን የባንክ ስሊፕ ይዘው በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትርበሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይበተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች ለሚገዙት ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) ነገርግን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር ያልበለጠ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
5. የጨረታው የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል፡፡ ይሁንና የተሽከርካሪውን የመነሻ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) ነገር ግን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር ያልበለጠ/
1. ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
6. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ ዕዳ ካለበት በባለንብረቱ መሥሪያ ቤት የሚሸፍን ሲሆን የጉምሩክ ቀረጥ ግብር እዳ፣ የስም ማዛወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
7. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመከፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት እያስቀረውም፡፡
8. ጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁንና ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል::
9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ተሸከርካሪዎች ሙሉ ከፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
10. አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል፡፡
11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመከፈል ተሸከርካሪውን በ10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
12. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- የኢፌዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት
ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ፦ የተቋማችንን ድህረ-ገጽ www.pps.gov.et ይጎብኙ
የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት
