Tender Detail

Tender Details

  • Company Rift Valley Children and Women Development Organization (RCWDO) (ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዲቨሎፕመንት ኦርጋናዜሽን)
  • Address ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ጉርድ ሾላ ኤ.ኤች. ኤፍ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 304 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-647 83 82
  • Websitehttps://riftvalley.org.et/
  • Deadline08 Jul 2026, 3:30 PM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-07-08 16:00:00
  • Categories Vehicle

ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዲቨሎፕመንት ኦርጋናዜሽን የድርጅቱን በዋናው መ/ቤት ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ የመስክ መኪኖቹን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::


በድጋሚ የወጣ የመኪኖች

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዲቨሎፕመንት ኦርጋናዜሽን የድርጅቱን በዋናው /ቤት ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ የመስክ መኪኖቹን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም፡-

ተጫራቾች፡-

1.     ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መኪኖቹ በሚገኙበት አድራሻ ጉርድ ሾላ ቴን ሲሰተር ህንፃ ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ::

2.     ተጫራቾች የሚገዙትን መኪና ወይም ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል:: የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል

3.     የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል::

4.     ተጫራቾች የመኪናውን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /column/ ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአኀዝና በፊደል ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ አዲስ አበባ ከተማ ጉርድ ሾላ ኤኤች ኤፍ ህንፃ 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304 በሚገኘው የድርጅቱ ዋና /ቤት አስተዳደርና ፋይናንስ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራጩ ወይም በተወካዩ መፈረም አለበት::

5.     ተጫራቾች ጨረታው በተለያዩ የማስታወቂያ ሰሌዳዎችና በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ አለባቸው::

6.     አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 03 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ 5 ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል::

7.     ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለአንድ መኪና የማይመለስ 500 ብር (አምስት መቶ ብር) እየከፈሉ ባሉት 07 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ሰባተኛው ቀን 630 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ:: ለተጨማሪ መኪና መጫረት ከፈለጉ ተጨማሪ ሰነድ መግዛት አለባቸው::

8.     የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በተለያዩ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 (ሰባት) የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በሰባተኛው ቀን ከቀኑ 930 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 1000 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፊት በድርጅቱ ዋና /ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል::

9.     ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነድ ጋርከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ::

10. ድርጅቱ ላሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ

በስልክ ቁጥር 011- 647 83 82/0920523734 ወይም በአካል በመምጣት መጠየቅ ይቻላል:: ቦሌ /ከተማ ወረዳ 6 ጉርድ ሾላ .ኤች ኤፍ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 304

 

አዲስ አበባ

ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዲቨሎፕመንት ኦርጋናዜሽን

Save Tender