Tender Detail

Tender Details

  • Company Federal Public Procurement Service (FPPS) (የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት)
  • Address 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: + 251 11 223740
  • Websitehttps://www.pps.gov.et/
  • Deadline28 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-07-28 10:15:00
  • Categories Materials

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን እና የገቢዎች ሚኒስቴር የሆኑ የተለያዩ ንብረቶች ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

ያገለገሉ ልዩልዩ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ

ሰነድ ቁጥር PPS/NVP-3FBI/12/10/2018

 

የኢ... የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን እና የገቢዎች ሚኒስቴር የሆኑ የተለያዩ ንብረቶች ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላል።

1.     በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ማቅረብ ያስፈልጋል።

2.     ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ ቢሮ በመምጣት የንብረቶች ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራ መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ በቴሌ ብር እና ሲቢኢ ብርን በመጠቀም የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

3.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 300 እስከ 1000 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ከላይ በተጠቀሰት /ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።

4.     ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።

5.     የጨረታው የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል። ይሁንና የንብረቶቹን የመነሻ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ነገር ግን ብር 100,000 /መቶ ሺህ/ ብር ያልበለጠ ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።

6.     የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 415 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን የመፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት እያስቀረውም።

7.     በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተግለፀላቸው 7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ ፈል ይኖርባቸዋል። ይሁንና ሙሉ ፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መከፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል::

8.     በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች ሙሉ ፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል ተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።

9.     አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።

10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመፈል ንብረቶቹን 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።

11. ገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- የኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ፡- የተቋማችንን ድህረ-ገጽ www.pps.gov.et ይጎብኙ

 

የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት

Save Tender