Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አዋሽ ፡ አፋር ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-13-97-49-27
  • Website
  • Deadline29 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2026-07-29 05:00:00
  • Categories Goods

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩከ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 22/11/2018 እና 25/1/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


ጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዋሽ ጉምሩክ //ቤት የጉምሩከ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት 22/11/2018 እና 25/1/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ //ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩከ //ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላከሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት ከአዋሽ ጉምሩከ //ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩከ //ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የጨረታ መስፈርቶች:-

1.     ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣

1.     ዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅሰቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስከርወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡

2.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 22/11/2018 እና 25/11/2018 / እስከ ጠዋቱ 345 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ //ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩከ //ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ፡፡

3.     ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንከ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ //ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4.    ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ///ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡

 

ተ.ቁ

የጨረታ ቦታ

የጨረታ አይነት

ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች

የዕቃዎች መመልክቻ ቀን በጋዜጣ ከመጣበት ቀን ጀምሮ እስከ

 

የጨረታው የመዝገቢያእና የመክፈቻቀንና ሰዓት

 

1

ቃሊቲ ///ቤት

 

ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ

 

ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ ፡ኤሌከትሮኒክስ ፣ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች! የእጅ ሰዓት፣ኮስሞቲክስ፣መነፅር፣ ጌጣ ጌጦች፣ ጠፍጣፋ ብረት! ላሜራ፥የወዳደቁ ብረቶችና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች

ለግልጽናለሐራጅ 22/01/2018እና 25/11/2018 .ም  ከጠዋቱ 4፡00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ 3:45

 

ለግልጽ ጨረታ22/11/2018 25/11/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 22/11/2018 እና 25/2018 ዓ/ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡

 

 5.     የጨረታው መከፈቻ ቦታ- በቃሊቲ ///ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል::

6.    ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋርየሚታሰብላቸዉ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ 3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

7.    አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተግለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል፡፡

8.     ከላይ በተ..7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች በጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

9.     //ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው!

 

የአዋሽ ጉምሩክ //ቤት

 

Save Tender