የእህል፣ የጥራጥሬ፣ የምግብ ዘይት እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች (NFI Kits) ግዥ
ክፍል 1፡ የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ (Invitation for Bids - IFB)
ለተከበራችሁ ህጋዊ አቅራቢዎች በሙሉ!
የሀረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት አደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት (ገዢው አካል) በክልሉ ለሚያስፈልግ የሰብአዊ ድጋፍ አገልግሎት የሚውሉ የእህል፣ የጥራጥሬ፣ የምግብ ዘይት እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን (NFI Kits) ህጋዊና ብቃት ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ (National Competitive Bidding - NCB) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን በአቅራቢዎች ዝርዝር (Supplier List) ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የ2017/2018 ግብር ከፋይነታቸውን የሚያረጋግጥ የነፃነት ደብዳቤ (Tax Clearance) ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በአደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ ያለው ከሆነ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ 16 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ግዢው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0915102271 እና 0913438803
የሀረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት አደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት
✨ messages.ai_summary
- Procurement of grain, pulses, cooking oil, and non-food item kits (NFI Kits) for humanitarian aid under National Competitive Bidding.
- Issued by the Harari People's Regional State Disaster Prevention and Food Security Office.
- Submissions due within 15 working days from the newspaper notice; tender closes on the 16th working day at 4:00 (morning) and opens the same day at 4:30 (afternoon).
- Bid document price: ETB 500, non-refundable.
- Requirements: renewed trade license, TIN, VAT registration certificate, tax clearance for 2017/2018, and proof of registration on the government supplier list.
