Tender Detail

Tender Details

  • Company Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
  • Address አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114420688
  • Websitehttp://www.mughercement.com.et/
  • Deadline01 Sep 2026, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceBirr 575.00 (non-refundable) including VAT
  • opening dateSep 01, 2026 10:00 AM
  • Categories Food And Beverage

Supply of pasteurized milk for employees for one year (184,764 liters) to Muger Cement Factory


የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ሙሲፋ/2Re-05/2018

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት ለሠራተኞች የሚውል ፓስቸራይዝድ ወተት ለአንድ ዓመት 184,764 ሊትር ውል ገብቶ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ዋና መስሪያ ቤት (90 ኪ.ሜ ሙገር) እና ታጠቅ ቅርንጫፍ (10 ኪሜ የሚያቀርብ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2018 ዓ/ም፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ገርጂ መንገድ በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ከሚገኘው የሙገር ሲማንቶ ፋብሪካ የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical industry Corporation Mughe Cerment Factory) ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶከመንቶቹ ጋር በማያያዝ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሀሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘ የፋብሪካው ግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

በጨረታው በዕለቱ ነሀሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።

ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ 011 442 0216
ፋክስ 011 442 0688
አዲስ አበባ

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ

✨ messages.ai_summary
Open tender for a one-year contract to supply 184,764 liters of pasteurized milk for employees, delivered to Muger Cement Factory headquarters and Tatek branch. Bidders must hold a valid trade license, VAT registration, and tax clearance.
Save Tender