Supply of pasteurized milk for employees for one year (184,764 liters)
የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሙሲፋ/2Re-05/2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት ለሠራተኞች የሚውል ፓስቸራይዝድ ወተት ለአንድ ዓመት 184,764 ሊትር ውል ገብቶ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ዋና መስሪያ ቤት (90 ኪ.ሜ ሙገር) እና ታጠቅ ቅርንጫፍ (10 ኪሜ የሚያቀርብ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2018 ዓ/ም፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ገርጂ መንገድ በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ከሚገኘው የሙገር ሲማንቶ ፋብሪካ የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical industry Corporation Mughe Cerment Factory) ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶከመንቶቹ ጋር በማያያዝ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሀሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘ የፋብሪካው ግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።በጨረታው በዕለቱ ነሀሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ 011 442 0216
ፋክስ 011 442 0688
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
