Tender Detail

Tender Details

  • Company የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address ሚዛን አማን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0471355629
  • Website
  • Deadline03 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ (የማይመለስ)
  • opening dateይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛዉ ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት
  • Categories Food And Beverage , Catering And Cafeteria Services , Services

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ግዥ በሎት 1- የአማን ሻይ ቡና እና የምግብ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ፤ በሎት 2፡- የሚዛን አማን ሻይ ቡና እና የምግብ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል ግዥበሎት 1- የአማን ሻይ ቡና እና የምግብ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ፤ በሎት 2፡- የሚዛን አማን ሻይ ቡና እና የምግብ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1.      ተጫራቾች በሚጠይቀው ዘርፍ የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin no) ያላቸዉ፣

3.     የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣

4.     የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸዉ፣

5.     የዘመኑን ግብር የከፈሉና ከግብር ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸው ከገቢዎች መ/ቤት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6.     ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር፣

ለሎት 1 የአማን ሻይ ቡና እና ምግብ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ብር 40,000 ብር/አርባ ሺህ/ ብር

ለሎት 2- የሚዛን አማን የሻይ ቡና እና ምግብ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ 40,000 ብር/አርባ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7.     ተጫራቾች ስለጨረታዉ ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘዉን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመምሪያዉ የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ።

8.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ዋናና ኮፒ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያዉ ከተመለከተዉ የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ገቢ መደረግ አለበት።

9.     ጨረታዉ ማስታወቂያ በወጣዉ 15ኛዉ ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይሆናል።

10.   መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 135 5629

 

የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of tea, coffee, and catering services for sector offices in Bench Sheko Zone, split into two lots: Aman and Mizan Aman. Bidders must hold a valid trade license, TIN, VAT registration, supplier certificate, and tax clearance.
Save Tender