የአዳማ ከተማ አትሌቲከስ ክለብ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓ.ም የምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ከተማ አትሌቲከስ ክለብ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓ.ም የምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች ሟሟላት ያለባቸው መስፈርቶች/የተጫረቾች መመሪያ/፡፡
- ማንኛውም ድርጅት ግለሰብ እና በዘርፉ የተሰማሩ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ህጋዊ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የነበረ እና ማሰረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ እና የተጨማሪ እሴት ታከሰ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመከፈል አዳማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሲንቁ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 105455161211 በማስገባት ጨረታው ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ አዳማ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለምግብ አቅርቦት 50000.00 /ሃምሳ ሺህ/ ብር በባንክ ቼከ የተረጋገጠ ሲፕእ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀን የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታው አይሰተጓጎልም ሆኖም 6ኛው ስራ ቀን በዓል ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻልን በታሽገ ኢንቨሎፕ ኮፒውን እና ኦርጅናሉን በተናጠል በማቅረብ አዳማ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ቢሮ 5ኛ ፎቅ በመቅረብ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- እትሌቲከስ ከለብ በአሰላ ካምፕ ለ100 አትሌቶች መመገብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ለእትሌቲከስ ምግብ በሚዘጋጅበት አደራሽ ውስጥ ከአልኮል መጠጥ፣ ከተለያዩ ሱስ አስደዛዥ ዕፆች ጭፈራ ቤት እንዲሁም ስፖርተኛን ሊረብሹ የሚችሉ የራቀ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በቂ የማድ ቤት እና የምግብ ቁሳቁስ ከበቂ የሰው ሃይል ጋር ያለው መሆን ይጠበቅበታል፡፡
- ተጫራቶች በ2018 ዓ.ም በዚህ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው እየሰሩ ያሉ መሆኑን የሚገልፅ የስራ ልምድ ከንግድ እና ገበያ አግልግሎት ፅ ቤት እና ሲሰሩ ከነበረበት ቦታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ - 0223311250/0911941978
የአዳማ ከተማ አትሌቲክስ ክስብ
✨ messages.ai_summary
Adama City Athletics Club seeks qualified bidders for food catering services for athletes for the 2019 budget year. Bidders must hold valid licenses, be VAT-registered, have relevant experience, and provide facilities capable of feeding 100 athletes at Asella camp.
