የእቃ/የአገልግሎት ግዥ ጨረታ
ለመጀመሪያ ጊዜ እና በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት፡-
ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የእቃ/የአገልግሎት ግዥ
- ሎት 1 ፀረ-ተባይ ማጥፊያ እና መከላከያ አገልግሎት ግዥ
- ሎት 2 የታረደ የፈረንጅ ዶሮ አቅርቦት ግዥ
- ሎት 3 የዓሣ አቅርቦት ግዥ
ሁለተኛ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የእቃ/የአገልግሎት ግዥ
- ሎት 4 የሥጋ አቅርቦት ግዥ
- ሎት 5 የገላ ሳሙና አቅርቦት ግዥ
ተጫራቾች የሚከተሱትን መመሪያዎች በማሟላት ተገባራዊ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2018 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የገቢዎች ከሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገርውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመከፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተበሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ እቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ስለ እቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት፡፡
- ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡
- ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም 20% ቀንሶ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ ጠዋት 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል። የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናንሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴክኒካል ሰነድ ግምገማ፣ ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ እና ናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት (60%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (40%) ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን ቴክኒካል ናሙና ግምገማ ሰነድ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሰነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ- ስልክ ቁጥር 011 5 53 07 67/011 5 15 73 37
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Open tender for goods and services procurement by Filwuha Services Enterprise. Items include pest control services, dressed chicken, fish, meat, and bath soap supply. Bidders must have valid 2018 trade license, tax clearance, VAT registration, and supplier registration with Ministry of Finance.
