የአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የቀላል፣ ከባድ ተሽከርካሪዎች እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ኢንሹራስ ዋስትና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የኢንሹራንስ ዋስትና አገልግሎት ግዥ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር አኮኃ/የተ/የግ/ማ/ግጨ/አግ/5/2018
የአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የቀላል፣ ከባድ ተሽከርካሪዎች እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ኢንሹራስ ዋስትና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አአብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. የኢንሹራንስ ዋስትና አገልግሎቶችን ዓይነትና የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም በኩባንው ዌብሳይት ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች ለሚወዳሩበት ኢንሹራንስ ዋስትና ሽፋን አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የገንዘብ መጠን ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር ብቻ) በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በዓባይኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም በማሰራት ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የመጫረቻ ኦሪጅናል እና ኮፒ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሸገው ዓባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ግዥና አቅርቦት ከፍል ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ለላይ ከዋለበትበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው 15 ተከታታይ ቀን አየር ላይ ይውላል፡፡
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዓባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበርበሚገኘው ግዥና አቅርቦት ከፍል ቢሮ ቁጥር 19 /15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
9. በጨረታው የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች በአማራ ከልል በዞን ከተሞች ቢያንስ 1/አንድ/ የኢንሹራንስ ዋስትና ሰጪ ቅርንጫፎች ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
10. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዓባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ግዥና አቅርቦት ከፍል ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት፣
በስልክ ቁጥር 0912993321/0918762298 በመደወል
email: abaycon21@gmail.com
Telegram:http://t.me/abayconstructionplc,
Web:www.abayconstruction.com
የአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
