በስኳር እንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የተለያዩ ለፀረ አረም እና ለፀረ ፈንገስ የእርሻ ኬሚካሎችን አቅራቢዎችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኦኩስፋ-3 / አግጨ-0037/2014 ዓ.ም.
በስኳር እንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀውን በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ነጋዴዎች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
የተለያዩ ለፀረ አረም እና ለፀረ ፈንገስ የእርሻ ኬሚካሎችን አቅራቢዎችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ/አዲስ የንግድ ፈቃድ፣የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ/መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2:30-6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
የግዥ ዋና ክፍል
ካሳንችስ ልማት ባንክ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግብይት ህንጻ ስድስተኛ ፎቅ
ኦሞ ኩራዝ፡-1 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮ
ስልክ ቁጥሮች፡- 0916 40 55 90/ 0920 71 17 49/ 0909 19 78 53/
አዲስ አበባ ካሳንቺስ ሰርቪስ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ኩራዝ
0916 04 17 11/0912 33 17 33
3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ቀጥሎ የተመለከተውን የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሠከረለት (CPO) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
3.1 የእርሻ ፀረ አረምና ፀረ ተባይ ኬሚካሎች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ነው።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ነሐሴ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ነሐሴ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
5. የዕቃዎቹ ርክክብ የሚፈፀመው አዲስ አበባ ካሳንቺስ መናኸርያ ተብሎ በሚጠራው ወይም ጨርጨር ስጋ ቤት ወረድ ብሎ የኦሞ ኩራዝ-3 ስኳር ፋብርካ መጋዘን ይሆናል።
6. ጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።
7. የጨረታው ማስረከቢያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ለ 90 ቀናት ነው።
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት
