Tender Detail

Tender Details


የዳግማዊ ምኒልከ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ለመግዛት ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ዳ/ም/ኮ/ስ/ሆ/04/2018

የዳግማዊ ምኒልከ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ለመግዛት ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

የጨረታ ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

ምርመራ

ሎት-01

የስልክ መስመር ዝርጋታ ግዥ

100,000

 

 

ሎት-02

የተለያዩ የጥገና ስራዎች ግዥ

100,000

 

 

ሎት-03

የፀረ ተባይ እና የፀረ ቆርጣሚ ርጭት አመታዊ ግዥ

50,000

 

 

ሎት-04

የፐላንት ማሽንና መሳሪያዎች እድሳትና ጥገና አገልግሎት ግዥ

100,000

 

በድጋሚ

 

በዚህም መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ፤

1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው

2. የዘመኑ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3. የቫት ተመዝጋቢነት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

4. የገቢዎች ከሊራንስ ጊዜው ያላለፈበት ደብዳቤ ያላቸው

5. በመንግስት ግዥ አቅራቢነት ለመመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው

6. በመንግስት ግዥ ያልታገዱ

7. የጨረታው ማስረከቢያ በCPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ቢድቦንድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

8. የጨረታ ማስከበሪያ ኦርጅናል ቴከኒካል ዶከመንት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 ብር በመከፈል በሆስፒታሉ የከፍያና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር B-008 (የዓይን ህከምና ማዕከል ህንፃ) በመቅረብ መግዛት ይችላሉ

10. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በዝርዝር ሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ/መሙያ ቦታ በግልጽ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 069 ማስገባት ይኖርባቸዋል'' ሆ/ሉ ካዘጋጀው የዋጋ መሙያ ውጪ ሌላ ቅፅ መጠቀም እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ማህተም የሌለው ሰነድ ከጨረታ ውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡

11. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም የቴከኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ብሎ በመለየት በአራት (04) በተለያዩ ፖስታ በማሽግ ፊርማና ማህተም ተደርጎ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ሆ/ሉ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

12. ጨረታው 10 የስራ ቀናት የአየር ላይ ቆይታውን እንዳጠናቀቀ በዘኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመከፈቻ እለቱ በዓል ቅዳሜና እሁድ/ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይበተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡

13. የጨረታ ማስከበሪያ በሎቱ በቀረበው መሰረት ነው፡፡

14. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈውን ስራ ሙሉ ስራ ሰርቶ ከፍያ እስከሚወስድ ድረስ ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንከ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድቦንድ ማስያዝ አለበት ፡፡

15. የሚገዙት ዕቃዎች/ ስራዎች በተሰጠው ስፔስፌስፊኬሽን መሰረት ተሟልተው ካልቀረቡ ካልተሰሩ ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው፡፡

16. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አ.አ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ዳግማዊ ምኒልከ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ

ስተጨማሪ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር 011-123-42 72/011-126-02 80/ 0952545405 ይደውሉ።

ዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Save Tender