ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት የመታሻ ዘይት (ፓራፊን ኦይል) አቅርቦት ግዥ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን ዕቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት፡-ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ/አገልግሎት ግዥ
- የመታሻ ዘይት /ፓራፊን ኦይል/ አቅርቦት ግዥ ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው
- ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2014 ዓ.ም. ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስhር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከአገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንድ ሎት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
- ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ሙሉ አድራሻቸውን፣ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን ለወጥ አይቻልም። እቃው የሚቀርብበት ጊዜ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መግለፅ አለበት ስለ እቃው የዋስትና ጊዜ በግልፅ መገለፅ አለበት።
- ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውዏ ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።
- ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 4/12/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ጠዋት በአለቱ 4፡30 ሰዓት ይከታል።
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል። የጨረታው ቴhኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናንሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ እስፔስፊኬሽን፣ ናሙና ጥራት እና ድርጅታዊ ብቃት ውጤት (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) ሲሆን ድምር ውጤት አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ። ነገር ግን እስፔስፊኬሽን፣ ናሙናውን ወይም ድርጅታዊ ብቃት ያላለፈ ፋይናንሽያል እንደማይከፈት እንዲታወቅ። የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ ስልክ ቁጥር፡- 011 551 9100/ 011 553 07 67 /011 515 7337
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
