ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ. በሬዲዮና በቴሌቪዥን የፋናን ብራንድ የያዘ ጥራታቸው ከፍ ያለ ፣ የሳቢነት እና በመልዕክት አቀራረፁና አቀራረቡ የተሻለ የማስታወቂያ ዝግጅት እንዲኖረው በዘረፉ ፍቃድ ያላቸውን የማስታወቂያ አዘጋጆችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
የቴሌቭዥን እና የሬዲዮ ፕሮዳክሽን ስራ ጨረታ ማስታወቂያ
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ. በሬዲዮና በቴሌቪዥን የፋናን ብራንድ የያዘ ጥራታቸው ከፍ ያለ ፣ የሳቢነት እና በመልዕክት አቀራረፁና አቀራረቡ የተሻለ የማስታወቂያ ዝግጅት እንዲኖረው በዘረፉ ፍቃድ ያላቸውን የማስታወቂያ አዘጋጆችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ የስራ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በዋናው መ/ቤት ደንበኞች አገልግሎት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ የማስከበሪያ ዋስትና bid bond 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank guarantee) ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራቾች የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ሰነድ ዋናውንና አንድ ፎቶ ኮፒ በተናጥል በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ እስከ ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 በማስመዝገብ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጉ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ፋና ብድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ.
