የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በማረቆ ልዩ ወረዳ የቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስተሪያል ኮሌጅ በ2016 ዓ/ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት
- የትምህርትና ስልጠና ዕቃዎች ግዥ
- የቢሮ የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ
- የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች ግዥ
- የኤልክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
- የተሸከርካሪዎች ግዥ
- የደንብ ልብስ ግዥ ሲሆን
ሁሉም የተጠቀሱት ዕቃዎች ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን ይገባቸዋል። ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ቲን ነምበር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ግዥና/ንብ/አስ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 15 በአካል ቀርቦ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ ብር 5,000(አምስት ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) በቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ስም በማሰራት ከጨረታው ሰንድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፍዎች ያሸናፉትን እቃዎች ናሙና /ሳንፕል ማቅረብ አለባቸው።
- ተሸናፊ ተጫራቾች (ድርጅቶች) ያስያዙት ገንዝብ / ሲፒኦ ውዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉትን ዕቃዎች ቆሼ ኮንስትራክሸንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ድረስ በራሳቸው ትራንስፓርት ማቅረብ ይኖረባቸዋል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየ ብቻ በማሸግ ሙሉ አድራሻቸውን በመግለፅ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ቀጥሎ ባለው በስራ ቀን ልክ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ 0464650672/0913939428/0934871934
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በማረቆ ልዩ
ወረዳ የቆሼ ኮንስትራክሸንና ኢንዱስተሪያል ኮሌጅ
