Tender Detail

Tender Details

  • Company አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን
  • Address , Phone: 033 312 91 72
  • Website
  • Deadline30 Jan 2024, 12:14 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Organizational

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2016


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት የሚውል 1ኛ 1ኛ. በከተማ ውስጥ ለሚያሰራው የመንገድ ስራዎች ሎደር ማሽን ኪራይ የኦፕሬተር አበል ውጭ፣የነዳጅ ውጭ፣የቅባትና ዘይት ወጭ፣ የሚከራዩ ማሽኖችን ከአንድ የስራ ቦታ ወድ ሌላ የስራ ቦታዎች የሚያስፈልጉ የማጓጓዥያ ወጭዎች፣እንዲሁም ሌሎች ወጭዎች አከራዩ ችሎ በሰአት ተከራይቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

2ኛ የተሽከርካሪ ማሽነሪ ዘይትና ቅባት፣ቢትመን፣ፕራይም ኮት እና የአስፓልት ፕላንት ሲቭ ብግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያJሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች ህጋዊና በዘመኑ የታደሠ የንግድ ወይም የስራ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ያላቸው።
  3. የግዥ መጠን ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴታ ክስት (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዞወ ማቅረብ አለባቸው።
  5. የሚገዙ እና የሚከራዩ ሎደር ማሽን ኪራይነት የተሽከሪካሪና ማሽኒሪ ዘይትና ቅባት ቢትመን፣ ፕራይም ኮት እና የአስፓልት ፕላንት ሲቭ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሠነዱ ማገኘት ይቻላል።
  6. የተሽከርካሪና ማሽነሪ ዘይትና ቅባት፣ ቢትመን፣ ፕራይም ኮት እና የአስፓልት ፕላንት ሲቭ ብር ወይም እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% ከነቫቱ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ(ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው። በጥሬ ገነዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘ ተጫራች የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል። ከጨረታ ሰንዱ ጋር የደረሰኝ ኮፒ ያላያያዘ ተጨራች መ/ቤቱ ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚያደረግ መሆኑን እንገልጻለን።
  7. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ግዥ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኃላ ለተጨማሪ 30 ቀናት ፀነቶ መቆየት ይኖርበታል።
  8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነዱ ማለትም ለሎደር ማሽን ኪራይ የማይመለስ ብር200.00/ሁለት መቶ ብር/ ለፕራይም ኮት እና ቢትመን የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ የአስፓልት ፕላንት ሲቭ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ የተሽከርካሪና ማሽነሪ ዘይትና ቅባት የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ሂደት ማግኘት ይቻላል።
  9. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለስልጣን ከግዥና ፋ/ንብ/አስ/የስ/ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁሉም ጨረታዎች ለተከታታይ 15 ቀኑ 11፡30 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል ጨረታው በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል።
  10. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ እስከ 15ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ አብሮ ማስገባት ይኖርበታል በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል። በ16ኛው ቀን የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲፒኦ ተቀባይኒት የሌለውና ተጫራቹን ከጨረታ ውድድር ውጭ መ/ቤቱ የሚያደርግ መሆኑን እንገልጻለን።
  11. ማንኛውም ተጫራቾች ያቀረበው የጨረታ ሰንድ ፓስታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪይ ወይም ሲፒኦ የሌለው ከሆነ በጨረታ ሰንዱ ላይ የሞላው ዋጋ ይማይነበብና ተጫራቹም ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚሆኑን እናስታውቃለን።
  12. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ መሙላት የሚችለው መ/ቤቱ ባቀረበለት ዋጋ መሙያ ሰንድ ብቻ ሲሆን በሌላ ወይም በራሱ የዋጋ መሙያ ሞልቶ ቢያቀርብ ተጫራቹን መ/ቤቱ ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚያደርግ እና በሁለት ዋጋ መሙያ ሞልቶ ያቀረብውን ተጫራች መ/ቤቱ በህግ ይሚጠይቅ መሆኑን እናሳውቃለን።
  13. ጨረታ ለሁሉም እቃዎች የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኚበት በደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል የሚከፈትበትን ቀን የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
  14. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ/ማሽነሪ/ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለስልጣን መ/ቤት ድረስ በራሱ ማጓጓዣ ማቅረብ ይኖርበታል።
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ለውል ማስከበሪያ የሚሆን 10% የሚያስይዝ መሆኑን እንገልጻለን።
  17. በጨረታ ለመሣተፍ የሚፈልጉና ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 312 91 72/ 033 311 10 41/10 48 10 59 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

አድራሻ፡ ካራጉቱ መስጅድ ፊት ለፊት

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን

Save Tender