በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ የሚያመርታቸውን ምርቶች ተደራሸነቱን በሁሉም ከልሎች ለማስፋፋት ተጨማሪ የምርት ወኪል አከፋፋይ ድርጅቶችን በጨረታ ቁጥር APPF/SP/03/16 አወዳድሮ ከአሸናፊዎች ጋር ውል በመፈራረም አብሮ መስራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለወኪል አከፋፋይነት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ
መስፈርቶችን በሟሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
1) ተጫራቾች በፀረ-ተባይ ንግድ የተሰማሩ እና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው::
2) ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፀውን ሰነድና መመሪያ አዳሚ ቱሉ ባለው የፋብሪከው ዋና መሥሪያ ቤት ንግድ መምሪያ ቢሮ ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ጂቡቲ ኤምባሲ ፊትለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ መግዛት ይችላሉ::
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ስም በማዘጋጀት በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በኢንሹራንስ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለጨረታው የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
5. ጨረታው የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ጂቡቲ ኤምባሲ ፊትለፊት በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የሚከፈት ይሆናል፡፡ የተጫራቾች በጨረታ መከፈቻ ቀንና ሰዓት ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጎልም፡፡
6. የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
7. ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡ አ.አ ማስተባበሪያ ስልክ ቁጥር 011 662 4656 አ/ቱሉ 0464419164 (ማዞሪያ): 0991589980 (ንግድ መምሪያ ፓ.ሣ.ቁ 1206 (አ.አ) 247 (አ/ቱሉ)
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚቱሉ
የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ
