ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2016 ዓ.ም በመደበኛ በጀት በከልል ስር ለሚገኙ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተማሪዎች አሰሚ በጨረታው ላይ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
1. በየዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውs
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
3. በሚሳተፉበት አቅርቦት ጨረታ ክፍል አግባብ ካለው የመንግሥት መ/ቤት ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ የአገልግሎት አቅርቦት እንደሚሰጡ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ!
4 ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሠመራ ትም/ ቢሮ ቁጥር 5 የጨረታውን ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ሀሳብ እና ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶችን በመለየት በ2 ኮፒ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.አ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 5 በ11ኛው የሥራ ቀን በ3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
9. ለአሸናፊው ተጫራች የሚከፈል ቅድመ ከፍያ አይኖርም፡ በመሆኑም አቅርቦቱን በተገቢ ሁኔታ በስፔስፊኬሽን መሠረት አቅርቦቱን ማቅረቡ ሲረጋገጥ 100% ከፍያ ወዲያው ይፈጸምለታል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር ቢሮ ቁጥር 5 በስልክ ቁጥር 033-666-01-26/033-666-01-23 በመደወል ማግኘት ይችላሉ
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ
ሠመራ
