የጨረታ ማስታወቂያ
አማራ ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ የደንብ ልብሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
|
ተ ቁ |
ዝርዝር መግለጫ |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን (በብር) |
|
1 |
ሸሚዝ ነጭ |
በቁጥር |
7,260 |
100,000.00 |
|
|
ሸሚዝ ሰማያዊ |
በቁጥር |
2,620 |
|
|
|
ቆዳ ጫማ የወንድ |
በቁጥር |
2,680 |
|
|
|
ቆዳ ጫማ የሴት |
በቁጥር |
670 |
|
|
|
ካልሲ |
በቁጥር |
3,250 |
ስለሆነም ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መወዳደር ይችላሉ::
■ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
■ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከለገሃር ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በሚወስደው መንገድ መብራቱን እንደተሻገሩ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት የአመልድ ህንፃ ግዥና ፋሲሊቲዎች አስተዳደር መምሪያ 20ኛ ፎቅ ላይ ከየካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የህንፃው ምድር ቤት ወለል ላይ በሚገኘው አዲስ አበባ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ / በመክፈል ማግኘት ይችላሉ::
■ ተጫራቾች የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ደብዳቤ (ጋራንቲ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
■ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሽገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀነ- 8፡ 00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው::
■ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካቲት 20 ቀን 2016 ከቀኑ 8:30 አማራ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋሲሊቲዎች አስተዳደር መምሪያ 20ኛ ፎቅ ይከፈታል::
■ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አማራ ባንክ አ.ማ
ከባንክ ባሻገር
