Tender Detail

Tender Details

  • Company የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
  • Address ጎንደር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0581-26-03-06
  • Website
  • Deadline15 Mar 2024, 11:39 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Organizational

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ


የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለጎንደር ከተማ አስ/ትምህርት መምሪያና እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት /ቤት አገልግሎት የሚውል፤

በሎት : የእንስሳት ከሊኒክ የህንጻ ግንባታ

በሎት 2 የተለያዩ ንባታ ቁሳቁሶች

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡-

ማቅረብ የምትች መረጃ፡-

1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው

2. የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3. የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው

4. የሚገዛው ቁሳቁስና የሚገነባው ግንባታ የገንዘብ መጠን 200,000/ ከሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል፡፡

5. የህንጻ ግንባታውን ለማሰራት ደረጃ 7እ ከዘያ በላይ ያሉ ኮንትራክተሮች

6. ተጫራቶች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7. በሎት 1 አንድና በሎት 2 የሚገነባዉን ግንባታና የቀረቡትን የግንባታ ቁሳቁሶች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኪሽን)

ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በባንክ የተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/መቶ ብር/ በመከፈል ጎን//አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 መውሰድ ይችላሉ፡፡

10. ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ በሆኑ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጎን//አስ/ ግዥና/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

11. ተጫራቶች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡

12. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው

13. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት በጎንደር ከተማ አስ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

14. ማንኛውም ተጫራች የሚቀርብ ቅሬታ ካለ ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን 5 የስራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

15 ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ጎን/ከተ/አስ/ ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመምጣት ወይም በስልከ ቁጥር 058 126 03 06 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡

16. የግንባታ ቁሳቁሱን በሚፈለግበት ወቅት ጎን//አስ/ገንዘብ መምሪያ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

17 ተጫራቾች መጫረት መወዳደር/የሚችሉት የንግድ ዘርፍ በሚመለከታቸዉ ይሆናል፡፡

18. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ማሳሰቢያ:- አሸናፊው ተጫራች የሚያቀርበዉ የቁሳቁስ ግዥ ኦርጅናልና በወጣው እስፔስፊኬሽን መሰረት ይሆናል፡፡

የሚፈጸመው የቁሳቁስ ግዥ ከበጀት አንጻር ሊቀንስ ወይም ሊጨምር የሚችል መሆኑን፡፡

የግንባታ ቁሳቁሱ ግዥ አሸናፊ የሚለየው በሎት ጠቅላላ ዋጋ ስለሆነ ፡፡ ከተዘረዘሩት የግንባታ ቁሳቁሶች ውስጥ አንዱን ያልሞላ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

Save Tender