የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ለሚኩራ ክ/ከ/ወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው አገልግሎት የሚወሉ ዕቃዎችን በ2ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለመከራየት ይፈልጋል፡፡ ማለትም፡- የስፖርት ትጥቅ፣ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ መኪና ኪራይ፣ የህትመት ሥራ፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የድንኳን ኪራይ፣ የሞንታርቦ ኪራይ፣ የጀነሬተር ኪራይ፣ የዲኮር ሥራ ለተለተያዩ ፕሮግራሞች አገልግሎት የሚወሉ ለሌማት ቱርፋት ማስተገበሪያ ስራ ግብአት የሚወሉ የእንቁላል ጣይ የ3 ወር ቦባይን ብራውን ዶሮ ስለሆነም መስፈርቱን የሚያማሉ ተጫራቾች እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡ ተወዳደሪ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
1. ተጫራቶች የታደሰ ንግድ ፈቃድ/ የንግድ የምዝገባ የምስከር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው (TIN number)::
2. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ/ ብር በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 ብር በመከፈል የካ አባዶ ገደራ ገዘኸኝ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘ ኮፒ በታሸገ ፖስታ የዋጋ ማቅረቢያ ዋናውን እና ቅጅ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በወረዳው ፋ/ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ሁሉም ተጫራቾች በተገኙበት በወጣ በዘኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡
5. ጨረታው ሁሉም ተጫራቾች በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው መወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
7. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፊውን ዕቃ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ የግዥ ቡድን በአካል ቀርበው ውል መግባት አለባቸው፡፡ አሸናፊው ውል ሳይዙ ዕቃ ጭነው ቢመጡ ወደ መጋዘን ማስገባት አይችሉም፡፡
8. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊው ለተሸናፊ በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ አንገልፃለን፡፡
9. ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-866-04-91 ደውሎ መጠቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- የካ አባዶ ገደራ ገዛኸኝ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ይገኛል፡፡
ማሳሰቢያ፡- እያንዳንዱ ሎት ለየብቻው ከነሙሉ መረጃው በፖስታ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ለሚኩራ ክ/ከ/ወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
