Tender Detail

Tender Details

  • Company በሕግ በመፍረስ ላይ ያለ የብሔራዊ መሐንዲሶችና ሥራ ተቋራጮች ድርጅት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913019601
  • Website
  • Deadline19 Mar 2024, 6:13 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Organizational

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 02/2016


በህግ በመፈረሰ ላይ ያለው የብሔራዊ መሐንዲሶችና ሥራ ተቋራጮች ድርጅት የኮንስትራሽን መሣሪያዎች፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች፣የተሽከርካሪ እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ / በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላል፡፡

2. የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ ኮተቤ በሚገኘው ብሔራዊ መሐንዲሶችና ሥራ ተቋራጮች ድርጅት ግቢ በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቹ ለመጫረት ከሚያቀርበው ዋጋ 10% የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /Bid Bond/ በባንክ በተመሠከረለት ቼክ /CPO/ በመ/ቤቱ ትክከለኛ ስም በማሠራት ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝና በፖስታው ላይ የተጫራቹን ስምና አድራሻ በመግለጽ እስከ ጨረታው መዝጊያ መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓም ከጠዋት 400 ስዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 2- ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ መጋቢት 19 ቀን 2016. ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ 430 ይከፈታል፡፡

5. በቂ የዋስትና ማሰከበሪያ CPO ያላስያዙ ተጫራቾች ኮሚቴው ከጨረታው የመሰረዝ መብት አለው::

6. የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያው ለአሽናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታ ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡

7. ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎችን የሚጫረቱ ተጫራቾች ማንኛውንም ያልተከፈለ የመንግስት ቀረጥ፤ ግብር፤ የስም ማዞሪያና ሌሎች ወጪዎችን ሙሉ በሙሉ የሚሸፈነው የጨረታው አሸናፊ ይሆናል፡፡

8. የጨረታው አሽናፊዎች በውጤቱ መሠረት ከፍያውን ከፈፀሙ በኋላ ያሽነፋባቸውን ንብረቶች 15 ቀናት ውስጥ አንስተው ማጠናቀቅ አለባቸው፣ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ሣያነሱ ቢቀሩ ለሚፈጠረው ችግር /ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡

9. ከላይ በተጠቀሰው 15 ቀናት ውስጥ ንብረቱን አጠናቆ ያልወሰደ ተጫራች የመጋዘን ኪራይ በቀን ብር 100.00 እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

10. /ቤቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ በለሚ ኩራ /ከተማ ወረዳ 13 ስልክ ቁጥር 0913019601

ከአራራት ሆቴል ወደ ወሰን እና ካራ በሚወሰደው አዲስ አስፋልት ከሰንሻይን ኮንስትራክሽን ሪል ስቴት

 ከፍ ብሎ አቤም ሆቴል ፊት ለፊት፡፡

በሕግ በመፍረስ የብሔራዊ

 መሐንዲሶችና ሥራ ተቋራጮች ድርጅት

Save Tender