በድጋሚ የወጣ የትራፊክ ደህንነት መቆጣጠሪያ ዕቃ ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መለያ ቁጥር መ.ደ.መ.ፈ.አ/002/2016 ዓ/ም
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ከዚህ በታች የዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. Solar powered traffic warning light
2. Alcohol Tester
3. Traffic stick light
4. Speed Gun
5. Operational body camera
6. Laptop
ተጫራቾች ትክከለኛ አቅራቢ ስለመሆናቸው ህጋዊ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆኑ ፤ የተጨማሪ እሴት የታክስ የምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት እና የጨረታ መሳተፈያ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ እና ላሸነፉበት እቃ የውል ማስከበሪያ ማሲያዝ የሚችሉ እንዲሁም ቋሚ የስራቦታ ወይንም ድርጅት ያላቸው ሆነው በቅድመ ምልከታ ወቅት ድርጅታቸውን ወይንም የሥራ ቦታቸውን ለማሳየት ፍቃደኛ የሆኑ ፡፡
1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በተቋሙ ስም የተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000000983997 ላይ በመከፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ በመንገድ ደህንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ስራ ክፍል በመቅረብ የጨረታውን ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ፡፡
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ ለተገለፁት ዕቃዎች ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ በባንክ በተመሰከረለት የከፍያ ትዕዛዝ (C.P.O) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ለሁሉም ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ዕቃ ከጠቅላላ ዋጋ 2 % ማስያዝ አለባቸው።
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፤ የሚወዳደሩበትን በግልጽ ኤንቨሎፕ ላይ በመፃፍ እና የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው እለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተቋሙ የመሰብሰቢያ አዳራሽ 8ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል፡፡የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩት ዕቃዎች የእያንዳንዱን ነጣላ ዋጋ እና ድምር ዋጋ VAT ጨምሮ ማካተት ይኖርባቸዋል፡፡ ተቋሙ ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ዕቃዎቹ መንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ስፔስፊኬሽን መሰረት ወይም በሚቀርበው ናሙ ጥራት ዋስትና አነስተኛ ዋጋ እና አጠቃሎ የማቅረብ ጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል ፤ የሚወዳደሩበት ዕቃ በፖስታ አሽጎ በፖስታው ላይ የሚወዳደርበትን ዕቃ እና የድርጅቱን ስም መፃፍ ግዴታ ነው።
6. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ በወጣው ስፔስፍኬሽን (መስፈርት) መሠረት የማቅረብ ግዴ ይኖረዋል፣
7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃ ቢያንስ የአንድ ዓመት ዋስትና መስጠት አለባቸው፣
8. ተጫራቹ ያሸነፈበት ዕቃ/ዕቃዎች በሙሉ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ መቅረብ ይኖርበታል፣
9. የሚቀርቡ ዕቃዎች በተቋሙ የበላይ ኃላፊ ኃላፊነቱ የተሰጠው አካል ስለ ዕቃው ትክክለኝነት ሲረጋገጥና አቅራቢ ህጋዊ ደረሰኝ ሲያቀርብ ከፍያው ይፈፀማል፣
10. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
12. በጨረታው የሚሳተፉ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በዘርፉ የሚሰሩ ድርጅቶች ብቻ መሆን አለባቸው፡፡
13. ኮፒ እና ኦሪጅናል ተለይቶ በኤንቨሎፕ በተናጠል (ለየብቻ) በፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርት የማያሟሉ አቅራቢዎች ከጨረታው ውጪ የሚደረጉ ይሆናል
14. በጨረታው ሳጥን መከፈቻ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ በተkሙ ዕውቅና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
አድራሻ
- ቂርቆስ ከፍስ ከተማ ወረዳ 08 ካሳንቺስ ኢሲሲ ኢንተርናሽናል ሆቴል አዳዲስ ህንጻ 4ኛ
የግዥና ፋይናንስ የስራ ክፍል
ስበስጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 09 55 37 98 29 ወይም 09 11 19 87 70 19
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት
