ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የአርሲ ዞን ማረሚያ ቤት ውስጥ ለሚገኙት የህግ ታራሚዎች የበሰለ ምግብ ወይምለምግብ አቅርቦት የሚውል ጥሬ እህል እና የተለያዩ ማጣፈጫዎችን እንዲሁም የማገዶእንጨት የ2017 ዓ.ም በጀት ከሃምሌ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታኅሳስ 30/2017 ዓ.ም ለ 6 (ስድስት) ወር ለሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት ማንኛውም ጨረታውን ለመካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ፡
1. ተወዳዳሪዎች የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ወይም ቢሮ ውስጥየተመዘገቡና የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እናአግባብነት ያለው 2016 የታደሰ የንግድ ሥራ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተመዘገቡ ወይም የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይመሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ከፍሎ ይህ ማስታወቂያ በአዲስዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዞን ማረሚያ ቤትአስተዳደር ፅ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በማረሚያ ቤትአስተዳደር ፅ/ቤት ውስጥ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደርአለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከመቶ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በተመሰከረለት ቼከእና የምግብ እህል ናሙና ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅቶ የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማህበራትቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ ካልተገኘ በጥሬ እህል እናወዳድራለን፡፡
7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ከፍት ሆኖበ16ኛው ቀን በስራ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት በዞን ማረሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤትተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የህግ ታራሚ ኮሚቴዎች እና የማረሚያቤቱ ጨረታ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ይከፈታል።
8. የዞኑ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅቶ የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማህበራትበማረሚያ ቤቱ ውስጥ በተዘጋጀው ማብሰያ ቤት ውስጥ ምግብ አብስሎ ማቅረብየሚችል።
10. ማረሚያ ቤቱ የሚገኝበት ከተማ በአርሲ ዞን አሰላ ማረሚያ ቤት ነው፡፡
ለበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0223311040/0913439972
በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን
የአርሲ ዞን ማረሚያ ቤት
