በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወዊያ
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥይፈልጋል፡፡
ቁሳቁሶቹም 6 ዓይነት ሲሆኑ እነርሱም፤
1. በእንጨት፤ በብረት በቆዳና በሸራ የተሠሩ ልዩ ልዩ ዓይነትና መጠን ያላቸው ወንበሮች፣ ቁምሳጥኖች፣ ኮሞዲኖዎች፤ዴስኮች፣ ጠረጴዛዎች፣ ኮፊ ቴበሎች፣ ሼልፎች፣ ባንኮኒዎች የበርና የመስኮት መቃኖች፣ የፅድና የዝግባ ማዕዘኖች፣የታንቡራታ በሮች፣ በእንጨትና በፋይዚት የታሸጉ እግር ያላቸውና የሌላቸው የጠረጴዛና የኮንፍረንስ ቴብል ቶፖች፣
2. ከአሉሚኒየም ፍሬም የተሠሩ በሮች፣ መስኮቶች (መስታዎት ያላቸው እና የሌላቸው) የአሉሚኒየም ዘንጎች የድንኳንብረቶች፣
3. የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች (ዴስክ ቶፕ፣ ላፕ ቶፕ ዩፒ ኤስ፣ ፕሪንተሮች፣) የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች፣ ማሽኖች
4. ያገለገሉ ፍሪጆች፣ ቦይለሮች፣ የባኞ ገንዳዎች፣ የቁም ሻወር ሣህኖች ፍሎረሰንቶች የሽንትቤት ሳህኖች ዊልቸርሳይክሎች ወዘተ፣
5. የተሰባበሩና የወላለቁ የተለያዩ ከእንጨት የተሠሩ ቁሳቁሶች
6. የተለያየ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ጎማዎች ናቸው፡፡
በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያትኮንዶሚኒየም፤ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተከርስቲያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት200 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታ ሰነዱ በቁጥር 1፣ እና 4 ቅጥር ግቢዎች ውስጥ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆንእየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት በሰምበታሸገ ኤንቨሎፕ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) ከያዘ ሲፒኦ ጋር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በክኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶበዚሁ pat: በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በጠ5ኛው ቀን ዕሁድወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ "ወይንም በከፊልየመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0930-79-64-13 ወይንም 0975-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
