የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በደብረብርሃንማረሚያ ቤት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የምግብ እህል ሸቀጣ ሸቀጥ የማገዶ እንጨት በርበሬ ቅመማ ቅመም እናየአትከልት አቅርቦት ለስድስት ወር ማለትም ከነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ/ም በግልፅ ጨረታአወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ::
1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin Number ማስረጃ ያላቸውና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% በጥሬ ገንዘብ ወይምበባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያሲዙ
2. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነትየተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የማይመለስ በብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር /መ/ቤቱ የአዘጋጀውን የጨረታ ሰነድመግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ህጋዊ የምግብ እህል ሸቀጣ ሸቀጥ የማገዶ እንጨት፣ በርበሬ፣ ቅመማ ቅመምና አትክልት ለእያንዳንዱየንግድ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን፡፡
5.የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብአለባቸው፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች ፖስታውን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገፖስታ በመምሪያው ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበትከ25/10/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/11/2016 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉመሆኑንና ጨረታው በዚሁ እለት በ09/11/2016 ከቀኑ 8:30 ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በማረሚያ ቤት ቅጥር ግቢተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8 አሸናፊው በየወሩ እንደ ህግ ታራሚዎች ብዛት አቅርቦቱ ሊጨምር ሊቀንስ የሚችል ሲሆን እንዲቀርብ
መምሪያው በሚገልፀው መጠን በየወሩ የሚቀርብ መሆኑን ፤ 9. የውድድሩ ሁኔታ በተናጠል በየዘርፉ በነጠላየሚወዳደሩ መሆኑን እና ተቋሙ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት፣
10. ለበለጠ መረጃ ካስፈለገዎት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መጠየቅ የሚችሉ ሲሆንበተጨማሪም በስልክ ቁጥር 011 681 17 92 መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን፡፡
የሰ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ
