የጎንደር ብቅል ኃ/የተ/የግል ማህበር በዋናነት ለሚያመርተው ብቅል እና ተረፈ ምርቶች መያዣነት የሚያገለግል የተለያየ መጠን ያላቸውን ከረጢቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል ወስዶ ማሰራት ይፈልጋል
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ብቅል ኃ/የተ/የግል ማህበር በዋናነት ለሚያመርተው ብቅል እና ተረፈ ምርቶች መያዣነት የሚያገለግልየተለያየ መጠን ያላቸውን ከረጢቶች በቋሚነት ለአንድ አመት በጥራት አምርቶ የሚያቀርብለት ኩባንያ በግልፅጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል ወስዶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉድርጅቶች ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት በጥንቃቄ አንብባችሁ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን እንድታስገቡእንጋብዛለን፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች
- ንግድ ፈቃዱ የታደሰና ከረጢት በማምረት ስራ የተሰማራ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማያያዝ
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ አገልግሎት መስጫ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር200.000.00 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በማያያዝ በታሸገኤንቨሎፕ አድርገው በጎንደር ብቅል ፋብሪካ ግዥ ክፍል ቢሮ ከ29/10/2016 እስከ 18/11/2016 ዓ.ምከረፋዱ 5:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ
- የምርት ማስረከቢያ ቦታው ጎንደር እንደመሆኑ መጠን የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስና የማጓጓዣወጪን ያካተተ መሆን አለበት፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በፋብሪካው ፋይናንስመምሪያ ገ/ያዥ ቢሮ ማግኘት ይቻላል፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ተጫራቾች በራሳቸው ችግር ባይገኙምበተገኙት ተጫራቾች ፊት በጎንደር ብቅል ፋብሪካ ንግድ መምሪያ በ18/11/2016 ዓ.ም ከረፋዱ በ5:00 ሰዓት ይከፈታል፤
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ በተነገረው በ5 ቀናት ውሥጥ ከፋብሪካው ጋር ውል መውሰድ ይኖርበታል፤
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው
- መሟላት የሚገባቸውን ሰነዶች (የንግድ ፈቃድ፤የዘመኑን ግብር የተከፈለበት መረጃ እና ሲፒኦና ሌሎችንመስፈርቶች ካልተሟሉ ውድቅ ይደረጋል ናሙና በፋብሪካው ግዥ ክፍል ማግኘት ይቻላል፤
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0582111234 /0913598563/ 0918064175/0930001110 ደውሎመጠየቅ ይቻላል፤
የጎንደር ብቅል ፋብሪካ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
