ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስ/ር ዞን የሰቆጣ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽ/ ቤት በ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት በከ/አስ/ሩ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የውቅር መስቀለ ክርስቶስ ቅርስ የጥገና ስራ ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይፈቃድ ያላቸው በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
ስስሆነም የሚከተሱትን መስፈርቶች የሚያሟሱ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የሚችሱ መሆኑንይጋብዛል።
1. በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤፤
3. የተጨማሪ እሴት ታስክ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒከመጫረታቸው ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ፣
5. የግንባታውን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን )ከጨረታ ሰነዱ ያገኙታል፣
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከግ/ፋ/አስ/ር ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይቻላል፣
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ
21 ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትምዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰ/ከ/አስ/ር/ግ/ፋ/ን/አስ/ር/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥንበ22ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚሁ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ጨረታዉ ተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በሰ/ከ/አስ/ር/ግ/ፋ/ን/አስ/ር/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፣
9 . መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
10. ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊ ከሆኑ የጨረታውን ውል ማስከበሪያ ያቀረቡትን የጠቅላላ ዋጋ ድምር 25% በጥሬገንዘብ ወይም በሲፒኦ በማስያዝ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፅ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥውል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የመንግስት ስራ ዝግ ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ጊዜይከፈታል።
12. ትጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሰ/ከ/አስ/ር/ግ/ፋ/ን/አስ/ር/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር
3 በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 0334401040/41 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የሰቆጣ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽ/ቤት
